FIFT CENT

FIFT CENT Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from FIFT CENT, Grocers, Sydney.

"በቃ ውሰዳቸው፣ እኔን ግን ሰላም ስጠኝ"“Just Take Them and Leave Me Alone”By Iranian artist, Raoof Haghighi.
10/11/2024

"በቃ ውሰዳቸው፣ እኔን ግን ሰላም ስጠኝ"
“Just Take Them and Leave Me Alone”
By Iranian artist, Raoof Haghighi.

 ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀዳሚ ስራቸው ዶክመንት የሌላቸውን / ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት ከሀገር ማስወጣት ነው ተብሏል።የትራምፕ ዘመቻ ቃል አቀባይ ካሮሊን ሌቪት እ...
07/11/2024



ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀዳሚ ስራቸው ዶክመንት የሌላቸውን / ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት ከሀገር ማስወጣት ነው ተብሏል።

የትራምፕ ዘመቻ ቃል አቀባይ ካሮሊን ሌቪት እንደገለፁት ትራምፕ በፕሬዚዳንትነት ስልጣናቸው ከሚወስዷቸው የመጀመሪያ እርምጃዎች መካከል አንዱ ዶክመንት የሌላቸው / ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት ለማስወጣት የገቡትን ቃል መፈጸም ነው።

ሌቪት ፥ ትራምፕ በአሜሪካ ህዝብ ዘንድ አስደናቂ የተባለ ድል ማስመዝገባቸውን ገልጸው " ይህ ድል ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው የገቡትን ቃል እንዲፈጽሙ ' ትዕዛዝ ' እንዲሰጡ ያስችላቸዋል " ብለዋል።

ይህም ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት / በገፍ ወደ መጡበት ሀገር መመለስ (ማስ ዲፖርቴሽን) እንደሆነ ጠቁመዋል።

አንዳንድ ሚዲያዎች ይህ ሰነድ አልባዎችን በብዛት ከአሜሪካ የማስወጣቱ /ማስ ዲፖርቴሽን/ ተግባር የትራምፕ የመጀመሪያው ቀን ስራ ይሆናል ብለዋል።

ትራምፕ በምርጫ ዘመቻቸው ወቅት ሰነድ የሌላቸውን ሰዎችን በሚመለከት " ከአሜሪካ ምድር ጓዛቸውን አስይዘን ወደ መጡበት እንልካቸዋለን " ሲሉ ቃል ገብተው ነበር።

አንዳንድ ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት ትራምፕ በስልጣን ዘመናቸው ቢያንስ ቢያንስ ከ15 እስከ 20 ሚሊዮን ሰነድ የሌላቸው ስደተኞችን ከአሜሪካ ለማስወጣት እቅድ አላቸው።

 #2   አንዳንዴ ዋጋው  ትንሽ ነው ብለን ሜኑ ሳናይ የምናዛቸው ነገሮች በኋላ ልብ ቀጥ የሚያደርጉ የሂሳብ ደረሰኝ ይዘው ሊመጡ ይችላሉ !  ይሄ ክፍያ ምናልባትም የአንድ ምስኪን የቤት ኪራ...
19/10/2024

#2

አንዳንዴ ዋጋው ትንሽ ነው ብለን ሜኑ ሳናይ የምናዛቸው ነገሮች በኋላ ልብ ቀጥ የሚያደርጉ የሂሳብ ደረሰኝ ይዘው ሊመጡ ይችላሉ ! ይሄ ክፍያ ምናልባትም የአንድ ምስኪን የቤት ኪራይ ዋጋ አልያም ወር የሚያዳርሰው የአስቤዛ ሂሳብ ሊሆን ይችላል ።

እናንተስ ምን ትላላችሁ ?

የጡት ካንሰር መንስዔዎችና ምልክቶች    |  የጡት ካንሰር ከቁጥጥር ውጭ በሆነ መንገድ በጡት ውስጥ ያሉ ሕዋሳት አድገው እና ተከፋፍለው ዕጢ ሲፈጥሩ የሚከሰት ሕመም ነው። የጡት ካንሰር በሴ...
19/10/2024

የጡት ካንሰር መንስዔዎችና ምልክቶች

| የጡት ካንሰር ከቁጥጥር ውጭ በሆነ መንገድ በጡት ውስጥ ያሉ ሕዋሳት አድገው እና ተከፋፍለው ዕጢ ሲፈጥሩ የሚከሰት ሕመም ነው።

የጡት ካንሰር በሴቶች ላይ ከሚከሰቱት የካንሰር ዓይነቶች አንዱ ሲሆን÷ በአብዛኛው ከ 50 ዓመት በላይ በሆኑ ሴቶች ላይ ይከሰታል፡፡

ሲጋራ እና አልኮል መጠቀም፣ ከልክ ያለፈ ውፍረት፣ የሆርሞን ወሊድ መከላከያ ወይም ሌላ የሆርሞን መድሃኒት ለረጅም ጊዜ መጠቀም እና የጨረር ሕክምና ለጡት ካንሰር መከሰት ምክንያቶች ናቸው::

በተጨማሪም በቤተሰብ ውስጥ የጡት ካንሰር መኖር፣ አለመውለድ ወይም የመጀመሪያ ልጅን ከ30 ዓመት በኋላ መውለድ፣ ከወለዱ በኋላ ጡት አለማጥባት፣ ከ12 ዓመት ዕድሜ በፊት የወር አበባ መምጣት እና ከ55 ዓመት ዕድሜ በኋላ የወር አበባ ዘግይቶ መቆም እንደ መንስዔ ሊወሰዱ ይችላሉ::

የጡት ካንሰር ምልክቶች ምንድን ናቸው?

በብዛት የሚስተዋሉ የጡት ካንሰር ምልክቶች በጡት መጠን ወይም ቅርጽ ላይ ለውጥ ማየት፣ የአተር መጠን ያለው እብጠት፣ በጡት ወይም በጡት ጫፍ ላይ የመልክ ወይም የቆዳ ለውጥ፣ ከቆዳው በታች እብነ በረድ የመሰለ ጠንካራ ቦታ መኖር ናቸው፡፡

በተጨማሪም ከጡት ጫፍ ውስጥ በደም የተበከለ ወይም ንጹህ ፈሳሽ መኖር፣ የተሰራጨ ዕጢ ከሆነ ደግሞ የደረትና የአጥንት ሕመም እና የመሳሰሉት ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡

የጡት ካንሰር ምርመራ ለማድረግ በዋነኛነት ማሞግራፊ፣ አልትራሳውንድ እና ፒኢቲ የተሰኙት ምርመራዎች የሚታዘዙ ሲሆን አጠራጣሪ ውጤቶች ሲገኙ ናሙና ተወስዶ ምርመራ ይደረግበታል::

ሕክምናን በተመለከተም ቀዶ ህክምና፣ ኪሞቴራፒ፣ የጨረር ሕክምና፣ የሆርሞን ቴራፒን ጨምሮ በርካታ የጡት ካንሰር ሕክምና አማራጮች እንዳሉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ መረጃ ያመላክታል፡፡

የጡት ካንሰር ታካሚዎች ወደ ጤና ተቋም ቀደም ብለው ከመጡ እና ህክምናው ከተሰጠ የመዳን ዕድሉ ከፍ ያለ በመሆኑ ማንኛውም ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ያለበት ሰው በፍጥነት የሕክምና ምርመራ ማድረግ እንዳለበት ባለሙያዎች ይመክራሉ።

የነጭ ሽንኩርት መድኃኒትነት1. ነጭ ሽንኩርት ስራን በትክክል ለማከናወን፣ የሰውነት ሕዋሳትን ጤናማ ለማድረግ ፣ድካምን ለማስወገድ፣ዕድሜን ለመጨመር፣በአይጥና በልዩ ልዩ ተባዮች የሚመጡትን ተስ...
19/10/2024

የነጭ ሽንኩርት መድኃኒትነት

1. ነጭ ሽንኩርት ስራን በትክክል ለማከናወን፣ የሰውነት ሕዋሳትን ጤናማ ለማድረግ ፣ድካምን ለማስወገድ፣ዕድሜን ለመጨመር፣በአይጥና በልዩ ልዩ ተባዮች የሚመጡትን ተስቦ በሸታዎችን ለመከላከል ነጭ ሽንኩርት መብላት በጣም ጠቃሚ ነው፡፡

2. ማንኛውም ሰው መጥፎ ሽታ ባለበት አካባቢ ለፅዳት ከመሰማራቱ በፊት ነጭ ሽንኩርት ከትፎ ቢበላ ከማንኛውም በሽታ ከሚያመጡ ተዋህሲያን ለመዳን ይቻላል፡፡

3. በቂ ሕክምና በሌለበት አካባቢ በቁስል ለሚሰቃይ ሕሙማን በነጭ ሽንኩርት ጭማቂ አጥቦ በቁስሉ ዙሪያ በመደምደም በፋሻ ወይም በንፁህ ጨርቅ በማሰር ሕመምተኛውን ለመፈወስ ይችላል፡፡

4. ነጭ ሽንኩርት ቀቅሎ እንፋሎቱን የካንሰርንና የቲቢ በሽታዎችን ለመከላከልና በሳንባ አካባቢ ብርድና ጉንፋን ለማዳን ፍቱን መድኃኒቱ ነው፡፡

5. ብርድ ብርድ በሚያሰኝ ሕመምና በተለይም በጥርስ ሕመም ለሚሰቃዩት ሕሙማን ሁለት ራስ ነጭ ሽንኩርት የውስጠኛውን ሽፋናቸውን በመላጥ በሁለቱም ጉንጫቸው በተለይም በተነቃነቀው ጥርስ በኩል ነክሰው ረዘም ላሉት ሰዓት ቢጠቀሙበት መልሶ መልሶ ይጠነክራል፡፡

6. ለአስም፣ ለጉሮሮ ክርካሪ ወይም ኮርታ ለተባለው በሽታ እንዲሁም ጉሮሮ ለማፅዳት የነጭ ሽንኩርት ጭማቂ በስኳር ወይም በማር መጠጣት የተፈተነ መድኃኒት ነው፡፡

7. ነጭ ሽንኩርት የራስ ምታትና የደም ብዛት ያለባቸው ሰዎች ከ3 እስከ 5 ቀናት በማከታተል ሦስት ሦስት ፍንካች በቀን ሦስት ጊዜ ቢበሉ ከድካምና ከደም ብዛት ሊፈወሱ ይችላሉ፡፡

8. በደም መርጋት ምክንያት ለሚሰቃዩ ፣የልብ በሽታን፣ የፊንጢጣ ኪንታሮትና የእግር ደም ሥር እብጠት varicose የተባሉትን በሽታዎች ለመከላከልና ለመዳን ነጭ ሽንኩርት በመብላት መፈወስ ይችላል፡፡

9. ነጭ ሽንኩርት የቆላ ቁስል፣ችፌን፣የጨጓራ በሽታን ወረርሽኝን ኮሌራን ሳይቲካን የቁርጥማትን ሕመምን እንደሚያድን የተረጋገጠ ነው፡፡

ሰላም እና ጤና ከእናተ ጋር ይሁን

ስለመሬት መንቀጥቀጥ ሲነሳ ትዝ ያለን የፈጠራ ውጤት ። ....ቻይናዊው Wang Wenxi ከጥቂት አመታት በፊት ዌንቹዋን እና ዩሹ በተባሉት የቻይና ግዛቶች ተከስቶ ጉዳት ያስከተለው የመሬት መ...
19/10/2024

ስለመሬት መንቀጥቀጥ ሲነሳ ትዝ ያለን የፈጠራ ውጤት ። ....
ቻይናዊው Wang Wenxi ከጥቂት አመታት በፊት ዌንቹዋን እና ዩሹ በተባሉት የቻይና ግዛቶች ተከስቶ ጉዳት ያስከተለው የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት በቦታው ነበር ።

እና ይህ ክስተት ካለፈ በኋላ ፡ ለቀጣይ ይህ አይነት የተፈጥሮ አደጋ ቢከሰት የራሴንና የሌሎችን ህይወት እንዴት ማዳን እችላለሁ በሚል ነበር ወደዚህ ፈጠራ የገባው ።...
እና የፈጠራ ሀሳቡ ተሳክቶለት ፡ የመሬት መንቀጥቀጥ የማይበግረው ( earthquake-proof bed ) ሰርቶ የፈጠራ ባለቤትነት ሆነ ።....
በመሬት መንቀጥቀጥ ስጋት ተነሳስቶ በ Wang Wenxi የተሰራው ይህ አልጋ ፡ በሰላም ጊዜ ሲታይ ፡ መደበኛ አልጋ ብቻ ይምሰል እንጂ በውስጡ የተወሳሰቡ የመሬት መንቀጥቀጥ ከመድረሱ ጥቂት ሰከንዶች በፊት ማወቅ የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች እና ሌሎች ነገሮች የተገጠሙበት ነው ።...
እንደጥራቱና በውስጡ እንዳለው ምቾት ዋጋው የተለያየ ቢሆንም ፡ ከ4000 ዶላር ጀምሮ በሚሸጠው በዚህ አልጋ ላይ ተኝተው ፡ እንቅልፍ ላይ እያሉ የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ፡ አልጋው በቅፅበት ውስጥ እኩል ይከፈልና የተኛውን ሰው በውስጡ በመደበቅ ፡ ከአልጋነት ወደ ግዙፍ ጠንካራ የብረት ሳጥንነት ይቀየራል ።...
ከዚህ በኋላ ህንጻው ቢፈርስ ላዩ ላይ ፍርስራሽ ቢከመር ፡ ከውስጥ ያለው ሰው ያለስጋት መቆየት ይችላል ። ይህ ብቻ አይደለም ፡ በዚህ በግዙፍ የብረት ሳጥን ውስጥ ፡ የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ ቁሶች ፡ ምንም እንኳን fire proof ከሆነ ማቴሪያል የተሰራ ቢሆንም ፡ ድንገት በውስጥ እሳት ቢከሰት በሚል የእሳት ማጥፊያ ፡ በጭስ ምክንያት እንዳይታፈን ፡ የጋዝ ማስክ ፡ የታሸገ ውሀ ፡ ደረቅና የማይበላሹ ምግቦች ፡ የንፅህና መጠበቂያ እቃዎች ጭምር በውስጡ ስላሉ ፡ ከመሬት መንቀጥቀጥ የተረፈው ሰው የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አግኝተው እስኪያወጡት ሳይራብና ሳይጠማ ለቀናት መቆየት ይችላል ማለት ነው ። ...
እስከዛ ደግሞ ፡ በአልጋው ላይ የተገጠሙት የራዲዮ ሲግናሎች ፡ ለአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ምልክት እየሰጡ ፡ ሳጥኑ ያለበትን ቦታ ይጠቁማሉ ። ...
ክስተቶችን ፡ ወደ መፍትሄና አዘል፡ ፈጠራ ለሚለውጡ ባለ ብሩህ አእምሮ ሰወች 🙏

ታላቁ ማንችስተር ዩናይትድ ዛሬ በአዝናኝ ጨዋታ ተቃራኒ ቡድን እንዳይፈናፈን እንዲህ ዘግቶ በመጫወት ያሸንፋል! ባያሸንፍ ይኸው ከብብቴ ፀጉር‼(የምላሴማ እንደ አሰልጣኙ ፀጉር አለቀ! )
19/10/2024

ታላቁ ማንችስተር ዩናይትድ ዛሬ በአዝናኝ ጨዋታ ተቃራኒ ቡድን እንዳይፈናፈን እንዲህ ዘግቶ በመጫወት ያሸንፋል! ባያሸንፍ ይኸው ከብብቴ ፀጉር‼(የምላሴማ እንደ አሰልጣኙ ፀጉር አለቀ! )

Ameen 🙏
15/10/2024

Ameen 🙏

''ጅል እዳ ነው አሉ"ሰውየው እኮ ነው ከጓደኞቹ ጋር ሆኖ እናቱ የሞተችበት ሰው ቤት ለቅሶ ሊደርሱ ሄደው አብ አብሽር እሷንም አላህ ይርሃማት ያንተ እናት እኮ እናት ነበረች ሲሉ ሰምቷል......
15/10/2024

''ጅል እዳ ነው አሉ"

ሰውየው እኮ ነው ከጓደኞቹ ጋር ሆኖ እናቱ የሞተችበት ሰው ቤት ለቅሶ ሊደርሱ ሄደው አብ አብሽር እሷንም አላህ ይርሃማት ያንተ እናት እኮ እናት ነበረች ሲሉ ሰምቷል................ ከዚያም በሌላ ቀን ሚስቱ የሞተችበት ሰውዬ ጋር ለቅሶ ሊደርስ ይሄዳል ለሰውየውም "አብሽር እሷንም አላህ ይርሃማት ያንተ ሚስት እኮ የሁላችንም ሚስት ነበረች " ብሎ አቧራ አስነስቶ ተመለሰ እላችኋለሁ..

No one can motivate you, unless you motivate yourself.
14/10/2024

No one can motivate you, unless you motivate yourself.

Address

Sydney, NSW

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when FIFT CENT posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category