Hatersata

Hatersata Religious You tube advertising

02/02/2026


ፆመ ነነዌ ቤተክርስቲያናችን ካወጀቻቸው ሰባቱ አፃማት ውስጥ አንዷ ነች ነነዌ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ታሪካቸው በስፋት ከተጻፈላቸው የሜሶፖታምያ ከተሞች አንዷ ናት፡፡

ብዙ የሥነ መለኲት ምሁራን ከዛሬዋ የሞሱል ከተማ በተቃራኒ ከባግዳድ ሰሜን ምዕራብ 350 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ እንደ ነበረች ይስማማሉ፡፡

በዚህች ከተማ የሚኖሩት ሰዎች የሚሠሩት ክፋትና ኃጢአት እጅግ ከመብዛቱ የተነሣ ጽዋው ሞልቶ መጥፊያቸው ስለ ደረሰ ለፍጥረቱ ርኅራኄ ያለው እግዚአብሔር ግን ንስሐ ይገቡ ዘንድ ነብዩ ዮናስን ልኮላቸዋል፡፡

ይህ ነብይ ከአሕዛብ ወደ አሕዛብ የተላከ ነብይ ነው፡፡ አላላኩም አንድ ነብይ ወደ እስራኤላውያን ተልኮ እንደሚያደርገው ለመገሰጽ ሳይሆን ወደ ንስሐ ይጠራቸው ዘንድ ነበር፡፡

ነገር ግን ነብዩ ወደዚያች ከተማ እንዲሄድ በእግዚአብሔር ቢታዘዝም ወደ ተርሴስ ሲኮበልል እንመለከተዋለን፡፡

ቅዱስ ጄሮም ነብዩ ለምን እንዲህ እንዳደረገ ሲናገር፡- “ዮናስ አሕዛብን ከመጥላቱ የተነሣ ሳይሆን መዳን ከእስራኤል እየራቀ መሆኑን በትንቢት መነጽር ሲመለከት ወደ ነነዌ አልሄድም አለ፡፡

ይኸውም ሙሴ ይህን ሕዝብ ከምታጠፋው እኔን ከሕይወት መጽሐፍህ ደምስሰኝ ያለው ዓይነት ነበር 《ዘጸ.32፡31-32》፡፡

ቅዱስ ጳውሎስም “ስለ እነርሱ እርሱ ቢረገም እንደሚመርጥ እንደሰማነው” ብሏል 《ሮሜ.9፡3》፡፡

በእርግጥም በዘመነ ሐዲስ አሕዛብ በክርስቶስ አምነው ሲጠመቁ እስራኤል ግን መጻሕፍትን ብቻ ይዘው ቀርተዋል፤ እስራኤል ነብያትን ብቻ ይዘው ሲቀሩ አሕዛብ ግን የነብያቱን የትንቢት ፍጻሜ ይዘዋል 《ማቴ.12፡42》፡፡

ልብና ኩላሊት ያመላለሰውን የሚያውቅ አምላክ ግን ዮናስ ላለመታዘዝ ብሎ እንዳላደረገው ስላወቀ በልዩ ጥበቡ ሲወስደው እናያለን፡፡

አስቀድሞ ታላቅ ነፋስን በመርከቢቱ ላይ አመጣ፤ ዮናስን የሚውጥ ታላቅ ዓሣ አሰናዳ፤ ቀጥሎም ዓሣው በየብስ እንዲተፋው አደረገ፡፡

ዮናስ ወደዚያች ከተማ ከደረሰ በኋላ ግን ምንም እንኳን የሦስት ቀን መንገድ ዙሮ መስበክ ቢጠበቅበትም የአንድ ቀን መንገድ ያህል ወደ ከተማይቱ ውስጥ ሊገባ ጀመረ፤ ጮኾም በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች አለ።

የነነዌም ሰዎች #እግዚአብሔርን አመኑ፤ ለጾም አዋጅ ነገሩ፥ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ። ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፤ እርሱም ከዙፋኑ ተነሥቶ መጐናጸፊያውን አወለቀ ማቅም ለበሰ፥ በአመድም ላይ ተቀመጠ። አዋጅም አስነገረ፥ በነነዌም ውስጥ የንጉሡንና የመኳንንቱን ትእዛዝ አሳወጀ፥ እንዲህም አለ፡- “ሰዎችና እንስሶች ላሞችና በጎች አንዳችን አይቅመሱ፤ አይሰማሩም ውኃንም አይጠጡ፤ ሰዎችና እንስሶችም በማቅ ይከደኑ፥ ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ይጩኹ፤ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ።

እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ ይጸጸት እንደ ሆነ፥ ከጽኑ ቍጣውም ይመለስ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?” ሰው ወዳጁ ጌታም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ፤ ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም።

አሁን ላይም እነደነነዌ ሰዎች ክፋት ሀጢያታችን በዝቶ የመጣ ትልቅ መከራ ና ችግር ደርሶብናል እና አባቶች እንዳዘዙን እንደነነዌ ህዝብ ማቅ ለብሰን ፆም ፀሎታችንን ከሰኞ 25_27ድረስ እናቀርባለን !!
የጭንቅ አማላጇ ልጅሽን ለምኚልን አሜን፫🙏

31/01/2026

ንሰሀ
የሰው ልጅ በደለ ለበደለው በደል ግን ማስተሰረያ የሚሆን ድንቅ እድል ተሰጠው ይህም ንሰሀ ይባላል በመፅሀፍ ቅዱስ ታሪክ የሚያስገርሙኝ ሰዎች አሉ እነሱም
1. የንጉሱ ዳዊት ታሪክ
ንጉሱ ዳዊት ሀጥያትን ሰራ ሀጥያቱም የከፋ ነበር የኦርዮን ሚስት ተመኘ መመኘት ብቻ አይደለም አብሯት አደረ አብሯት ማደር ብቻ አይደለም ልጅ ወለደ ልጅ መውለድ ብቻ አይደለም ኦርዮንን አስገደለ።
2. የጳውሎስ ታሪክ
3.የሶምሶም ታሪክ
4. የማርያም መግደላዊት ታሪክ

30/01/2026

‹‹ጥር 22›› በዚችህ ዕለት የሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል ዓመታዊ በዓለ ሲመቱ ነው።

ዑራኤል የስሙ ትርጓሜ "የብርሃን ጌታ፣ የአምላክ ብርሃን" ማለት ነው።

ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ በመሆን ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ ነው።

ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ ክቡር ደሙን በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ በብርሃን መነሳነስ በዓለም ላይ የረጨ መልአክ ነው።

ለነቢዩ ዕዝራ ስቱኤል ጽዋ ጥበብን ያጠጣ መልአክ ነው።
ሰማያዊውን ዕውቀትና ጥበብ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የገለጠ መልአክ ነው።

ለነቢዩ ሄኖክ የሰማይን ምሥጢርና ሰማያዊውን ዕውቀት የገለጠ መልአክ ነው።

ቅዱስ ዑራኤል የፀሐይን፣ የጨረቃን፣ የከዋክብትንና የሠማይ ሰራዊትን ብርሃንን የሚመራ መልአክ ነው።

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል በምልጃው አይለየን🙏

ጥር 21 የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት“ ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ”ጥር 21 በዓለ አስተርእዮ (የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት)እንኳን ለዚህች ታላቅ በዓሏ አደረሰን፡፡ወላዲተ ...
28/01/2026

ጥር 21 የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት
“ ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ”
ጥር 21 በዓለ አስተርእዮ (የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት)
እንኳን ለዚህች ታላቅ በዓሏ አደረሰን፡፡

ወላዲተ አምላክ ምንም እንኳን የአምላክ እናት ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፈንታ በመሆኑ በስድሳ አራት አመቷ ከሞት ወደ ሕይወት ከመከራ ወደ ደስታ የተሸጋገረችበት ዕለት ነው፡፡
ታላቁ የቤተክርስቲያን አባት ቅዱስ ያሬድም “ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ” ትርጉሙ ሞት ለማናኛቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል፡፡ በማለት አደነቀ፡፡ በመሆኑም በዓሉ የወላዲተ አምላክ በዓለ ዕረፍት ከመሆኑ የተነሳ ታላቅ በረከት የሚያስገኝ ስለሆነ በየዓመቱ ይከበራል፡፡.. የእረፍቷስ ነገር እንደምን ነው ቢሉስድሳ አራት ዓመት በዚህ ዓለም ኖራ ጥር 21 እሁድ ቀን ጌታ እልፍ አዕላፋት መላዕክቱን አስከትሎ መጥቶ እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጣሁ አላት፡፡ ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህጸኔ ተሸክሜ በድንግልና ወልጄህ እሞታለሁミ አለችው፡፡ በሲዖል የሚሰቃዩ ነፍሳትን አሳይቶ እናቴ ሆይ ሞትሽ ለእነዚህ ቤዛ ይሆንላቸዋል አላት፡፡ እኚህን ከማርክልኝስ ይሁን አለችው፡፡ ቅድስት ሥጋዋን ከቅስስት ነፍሷ ለይቶ በቃለ አቅርንት በዝማሬ መላእክት አሳረጋት፡፡ ደቀመዛሙርቱንም ከያሉበት በደመና ጠቅሶ ካለችበት አድርሶ እመቤታችሁን ቅበሩ አላቸው፡፡ ባባ ይዘወት ወደ ጌሰማኒ ሲስደት አይተው ልጇን ተነሳ አረገ እያሉ ሲውኩን ይኖራሉ አሁን ደግሞ እሷን ተነሳች አረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለም ብሎ ኑ እናቃጥላት ተባባሉ፡፡ ከመካከላቸው አንዱ ታውፋንያ ዘሎ ያልጋውን ሸንኮር ያዘ፡፡ የታዘዘው መላእክት መጥቶ በሰይፍ ሁለት እጁን ቀጣው፡፡ በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማጸናት ድኖለታል፡፡ ከዚህ ቦሃላ ዮሐንስን ጨምሮ ከመካከላቸው ነጥቆ በእጸ ሕይወት ሥር አኑሯታል፡፡
አንድም በዓሉ-፡ እግዚአብሔር ወልድ በሰውነት ተወልዶና ማንነቱ በይፋ ታውቆ በተገለጠበት በዘመነ አስተርእዮ ውስጥ ስለሚከበር የ“አስተርእዮ ማርያም” ተብሏል፡፡ አስቀድመው አሥራ ሁለቱም ሐዋርያት ለስብከተ ወንጌል ወደ ዓለም ሁሉ ተበትነው ነበርና በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ሁሉም ደመናን ጠቅሰው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፡፡ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ መርቶ አመጣቸው እንጂ ለምን እንደመጡ አያውቁም ነበር፡፡ እመቤታችንም ለምን እንደመጡ ጠየቀቻቸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም፡- “ጸጋን የተመላሽ ቅድስት ሆይ! የመምጣታችን ምሥጢርማ እኛ አንቺን እንጠይቅ እንጂ አንቺም እኛን ትጠይቃለሽን? ሁላችንም ለምን እንደመጣን አናውቅም፡፡ ለምሳሌ እኔ አስቀድሜ በአንጾክያ ነበርኩኝ አሁን ግን እነሆ እዚህ ነኝ፡፡ ለምን እንደመጣሁኝ ግን አላውቅም” አላት፡፡ እርሷም ሁሉም በአጠገቧ በተሰበሰቡ ጊዜ የሚሆነውን ነገር አስቀድማ ከልጇ ከወዳጇ አውቃ ተዘጋጅታ ነበርና ለምን እንደመጡ (ዕረፍተ ሥጋዋን ለማየት እንደሆነ) ነገረቻቸው፡፡ ሌሊቱንም በሙሉ በጸሎትና በማኅሌት ደግሞም በዝማሬ ሲያመሰግኑ አደሩ፡፡ ከዚህ በኋላ የተወደደችው እናት በረከቷን አሳድራባቸው በሰላም አንቀላፋች፡፡ ነፍሷም በዐብይ ዕልልታና በታላቅ ምስጋና በመላእክት እጅ ወደ አምላኳ ሄደች፡፡ ኋላ ሐዋርያቱ ዮሐንስን ሲያገኙት፡- “እመቤታችን እንደምን ሆነች?” አሉት፡፡ እርሱም “በገነት በዕጸ ሕይወት ሥር ዐርፋለች” አላቸው

20/01/2026

ቃና ዘ ገሊላ (x2)
በዛ በሰርግ ቤት ተገኝተሻል ድንግል
ከልጅሽ ጋራ
ተገኝተሀል ጌታ ከእናት ጋራ
እልልልልል በሉ እስቲ

20/01/2026

‹‹ጥር 12›› "ቃና ዘገሊላ" በሰርጉ ላይ ጌታችን ከደቀ መዛሙርቱና ከእናቱ ጋር ተገኝቶ ውሃውን ወይን ጠጅ ያደረገበት ነው።

ሰርግ ደግሶ የነበረው #ዶኪማስ አዘጋጅቶት የነበረው ወይን ጠጅ አልቆ በተጨነቀ ጊዜ ችግሩን ቀርቦ ሳይነግራት ማለቁን አውቃ ልጄ ሆይ ወይን ጠጅ እኮ አልቆባቸዋል በማለት ተናግራ ውሃው ወደ ወይን ጠጅ እንዲለወጥ የማማለድ ተግባር የፈጸመችበት ዕለት ነው።

ጥንተ ዕለቱ የካቲት 23 ቀን ቢሆንም ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን የውሃን በዓል ከውሃ በዓል ጋር ማክበር ይገባል ብለው የሚጠጡት አልቆባቸው ተጨንቀው የነበሩበት ቃና ዘገሊላ የውሃ በዓል በመሆኑ ከውሃ በዓል ከሆነውና የእዳ ደብዳቤያችን ከተደመሰሰበት ከጥምቀት ጋር እንዲከበር በማድረጋቸው በዛሬው ዕለት እናከብረዋለን።

ዛሬ የዶኪማስ ጭንቀት ብቻ ሳይሆን በጋብቻ ምክንያት የሚከሠት የክርስቲያኖች ሁሉ ጭንቀት የተቃለልበት ዕለት ነው።

እመቤታችን ዶኪማስ ሳይለምናት ጭንቀቱን እንዳቃለለችለት ለልጅሽ አሳስቢልን ብለን ብንማጸናት የማይፈጸምልን ነገር፣ የማይወገድልን ጭንቀት አለመሆኑን የተረዳበት ዕለት ነው።

ከበዓሉ በረከት ያሳትፈለን🙏

20/01/2026

Warri Taabotni Muka Nun Fayyadu Jettan Wangeellis Waraqaadha Sin hin fayyadu mii???????????? 👇👇👇

Shakkitoonni, “Mukti maal nuuf godha? Waraqaan maal nuuf godha?” jedhu. Kun hubannoo dhabuu dha. Waaqayyo yeroo baay’ee humna isaa wantoota lafa irraa (Matter) keessaan ibsa:

• Uffata Qulqulluu Phaawuloos: Uffanni Phaawuloos dhukkubsataa fayyisa ture (H.D.B. 19:11—12).

• Lafee Raajicha Elsaa’ii: Lafeen isaa nama du’e kaaseera (2 Moot. 13:21).

• Muka: Museen uleedhaan Galaana Eertiraa hireera (Bau. 14:16).

• Bishaan: Dhiqannaadhaan Naa’imaaniin “Yordaanositti dhiqadhu” jedhamee bishaanichi isa fayyiseera (2 Moot. 5:14).

• Fiixee Uffataa: Dubartiin dhiigni dhiigaa ture, fiixee uffata Gooftaa tuqxee fayyiteetti (Maat. 9:20).

Egaa, uffata, lafee, mukaa fi bishaan keessan humni Waaqayyoo yoo darbe; Taabota Maqaan Waaqayyoo irratti bocamee fi dhiigni Gooftaa irratti qophaa’u keessaan akkamitti humni hin darbu? Taabotni “Iddoo Waaqayyo itti argamu” (Locus of God’s presence) dha.

Walumaagalatti, Taabotni Eenyummaa Itoophiyaa fi Mallattoo Kiristiyaanummaa ti. Obboloota koo, Manni Kiristiyaanaa Ortodoksii Tewaahidoo Taabota kan kabajjuuf Waaqayyo waadaa galeefii dha malee, muka waaqessuuf miti.

• Mootummaan Waaqayyoo Israa’el irraa fuudhamtee saba biraaf (Itoophiyaaf) kennamteetti (Maat. 21:43).

• Qulqulluun Yohaannis Mul’ata isaa irratti Taabota Samii keessatti argeera; nutis lafa irratti fakkeenya isaa qabna (Mul. 11:19).

• Taabotni bakka Maqaan Waaqayyoo (Alphaa fi Omeegaa) jiru dha; iddoo Maqaan isaa jiru immoo Waaqayyo jira.

• Iyyaasuun Taabota duratti kufee sagadeera; kun waaqeffannaa tolfamaa osoo hin taane, ulfina Waaqayyoo ti (Iya. 7:6).Kanaafuu, Taabotni Itoophiyaa jiraachuun isaa, mallattoo Waaqayyo saba kana akka jaalatee fi kakuu isaa akka nuuf kenne agarsiisa. Taabotni keenya mallattoo Kakuu Haaraa, Teessoo Fooniif Dhiiga Kiristoosii fi Iddoo Araaraa ti. Manni Waaqayyo samii irratti Taabota qabaannaan, nutis ijoolleen isaa laf

19/01/2026

‹‹ጥር 11›› "ጥምቀት" ማለት አጠመቀ ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ነው። ትርጉሙ መነከር፣ መደፈቅ፣ መጠመቅ ማለት ነው።

ቅዱስ ዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ እያጠመቀ ሳለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመጥምቁ ዮሐንስ እጅ ይጠመቅ ዘንድ ወደ እርሱ ሄደ

" ...ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ።"
ማቴ. ፫፥፲፫ /3፥13/
ቅዱስ ዮሐንስም "እኔ በአንተ ልጠመቅ ሲገባ አንተ ወደ እኔ ትመጣለህን" ብሎ ጠየቀው

ሁሉን አዋቂው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን "ጽድቅን ሁሉ ልፈጽም ዘንድ ይገባል" በማለት ለእኛ አርአያ ለመሆን ሲል ወደ አገልጋዩ ዮሐንስ ዘንድ በመሄድ ተጠመቀ

ተጠምቆም ሲወጣ የምወደው ልጄ ይህ ነው በማለት አብ መሰከረ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ ተቀመጠ።

እኛም ለዘመናት ይህንን የጌታችንን በዮርዳኖስ ወንዝ መጠመቅ መሠረት በማድረግ በየዓመቱ በዓሉን እናከብራለን።

ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን🙏

19/01/2026

ታይተን ገብተናል ተቈጥረን ተመልሰናል"
👉 ዘመኑ ገሃድ ይባላል በሌላም አስተርዕዮ ይባላል ሁለቱም ግን ትርጕማቸው መገለጥ ማለት ነው ይህም የመገለጥ ዘመን ክርስቶስ በሥጋ የተገለጠበትና አንድነት ሦስትነት የተገለጠበት ወርኅ ነው በዚህም ኦርቶዶክሳውያን ነጭ ለብሰው ነጭ ጠምጥመው፡ ሊቃውንቱ ነጭ ካባ ደርበው ነጭ ሻሽ ጠምጥመው ነጭ ጋቢ ለብሰው ነጭ ጫማ ተጫምው መላእክትን መስለው በበዓለ ጥምቀቱ ደምቀው እንደ ከዋክብት አሸብርቀው ይገለጣሉ። ይህም ፍጹም ደስታን መግለጥ ነውና መልካም ነው።

ነገር ግን ጥያቄ መጠየቅ እፈልጋለሁ?!
፩, ዓመቱን ሙሉ ቤተክርስቲያን መጥቶ የማያውቅ በዚህ ዕለት ብቻ የሚወጣ ምዕመን አለ ለዚህ ቤተክርስቲያን ምን ተልእኮ ሰጥታ ትሰዳለች ?
ምክንያቱም በዚህ እለት መንግሥት የራሱን መልእክት በማስተላለፍ ሰፊውን ጊዜ ይይዘዋል ወጣቱ ዙሪያውን ሆሆሆሆሆሆ እያለ ይጨፍራል ግማሹ ጎን ለጎን እየተለካከፈ ሎሚ ይወራወራል....... ለዚህ ቤተክርስቲያን በራሷ ዓውደ ምህረት ለራሷ ልጆች የራሷን መልእክት ካላስተላለፈች የጥምቀት በዓሉ ምኑ ላይ ነው?

፪, ይህ ሁሉ በሚልየን የሚቆጠር ክርስቲያን እጅግ እጅግ የነጻ ልብስ ለብሶ ወጥቶ አክብሯል ነገር ግን ይህ ሁሉ ምን ያህሉ በንስሃ ውስጡን ብሩህ አድርጓል? ያም ካልሆነ ዘመኑ ዘመነ ንስሓ እንደመሆኑ ወደፊት ንስሓ እንዲገባና እንዲመለስ በየትኛው ባሕረ ጥምቀት አብዛኛውን ጊዜ ለስብከተ ወንጌል ተሰጥቶ የንስሓ ስብከት ተደርጓል?

፫, ከጥምቀተ ባህር ደርሶ ከተመለሰ በኋላ ራሱን በስሜታዊ ደስታ ውስጥ አስገብቶ ራሱንም እንደ ጻድቅ ቆጥር ታቦተ ሕጉ ስንኳን ወደ መንበሩ ሳይመለስ ጃንቦ ቤቶቹንና ጭፈራ ቤቶቹን ሞልቶ እንዲያውም ከአንድ አንድ ከተሞች መስመሮቹ ሳይቀር የመጠጥ አዳራሾች እስኪመስሉ ድረስ እብደት በተሞላበት ቅሌት በጭፈራም በመጠጥም ሰክሮ የሚያመሽ ኦርቶዶክስ ለምን ተፈጠረ?

፬, የማይበጠስ ኦርቶዶክሳዊ ሰንሰለት ያለውና ከዓላማው ዝንፍ የማይል ክርስቲያን መፍጠር ሳይቻል የጥምቀትና የመስቀል ብቻ ወጥቶ ዘምሮና እልል ብሎ እረኛ እንደሌለው በግ የሚበተን ክርስቲያን ለምን ተፈጠረ?
ሊቃነ ጳጳሳትስ በቅርብ አማካሪዎቻቸው ተከሽኖ የተጻፈላቸውን መልእክት አትሮንስ ላይ ዓይናቸውን ተክለው አንብበው ይህንን በነቂስ የወጣ ሕዝብ ከመበተን ለምን አንብበው ተርጕመው አባታዊና ወንጌላዊ ትዕዛዝ አዝዘው የቤት ስራ አይሰጡትም?
ያም ካልሆነ የተሻሉ መምህራንን ጋብዘው ጠንከር ጠጠር ያለ ትምህርት እንዲማርና በቤተክርስቲያን ድርሻውን እንዲወስድ ለምን አላደረጉትም?

፭, ክርስቲያኑ በዓላትን የበዓል ልብስና የበዓል ድግስ እያለ ክርስቲያናውያን በዓላትን የሆድና የልብስ በዓላት አስመስሎ እስኪውል ድረስ የቤተክርስቲያን መዋቅር መሪዎችና አገልጋዮች ምን እየሰራን ነው?
(የአይጥ መንጋ ድመት እስኪመጣ ነው) እንዲሉ በዝተን ለምን አነስን? ብርቱዎች ሆነን ለምን ደከምን? ነጭ ለብሰን ውስጣችን ለምን ጠቆረ? ዕውቀት አልባ ስሜት ለምን በልቡናችን እንዲመነጭ ሆነ?
ክርስትናችንስ በዓመት ውሱንጊዜ ብቻ እንዲጎላ ሆነ?

፮, በቤተክርስቲያን ውስጥ ለስላሳ የሆነ ክርስቲያን ለምን ተፈጠረ? ይህም ማለት፦ መዘመር የሚወድ ቀኖና የማይወድ፡ እልል ማለት የሚወድ ጠንከር ያለ ትምህርት የማይወድ፡ መጾም የማይወድ በበዓል ስም ደግሶ መብላት የሚወድ፡ ነጭ ለብሶ መውጣት የሚወድ ልቡን በንስሓ ማንጣት የማይወድ፡ ተግሳጽ የማይወድ ከንቱ ውዳሴ የሚወድ፡ አንድ ሰዓት ቆሞ ወንጌል መስማት የማይወድ አምስት ሰዓት መጠጥ ቤትና ጭፈራ ቤት ቁጭ ማለት የሚወድ፡ ማስመሰል የሚወድ መሆንን የሚጠላ ለስላሳ የ

19/01/2026

ቃና ዘገሊላ በቀጥታ ትርጉም የገሊላዋ ቃና ማለት ነው፡፡ እንደ ቤተክርስትያን አስተምህሮ በጥምቀት በዓል ማግስት (ጥር 12) ቀን የቃና ዘገሊላ በዓል ይከበራል፡፡

ይህ በዓል ከጌታ ጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ በድምቀት የሚከበር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዳራ ያለው በዓል ነው፡፡ በዓሉ ቃና
ዘገሊላ የሚል ስያሜ ያገኘው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ሀገር ክፍል በምትሆን ቃና በተባለችው ቦታ በፈፀመው ተአምር መነሻነት ነው፡፡ የቃና ዘገሊላ ጥንተ ነገሩ ወይም ታሪኩ የተፈፀመው የካቲት 23 ቀን ነው፡፡ ነገር ግን አባቶቻችን የውኃን በዓል ከውኃ በዓል ጋር ለማክበር ብለው የየካቲቱን በዓል ወደ ጥር 12 አምጥተውታል፡፡ ይህም ውኃ ወደ ወይን የተለወጠበትን በዓል ከጌታ ጥምቀት በዓል ጋር ለማስተሣሠር ለማስኬድ ነው፡፡ በመሆኑም የቃና ዘገሊላ በዓል ጥር 12 ቀን ይከበራል፡፡

?
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ክፍል በምትሆን በቃና በተደረገ ሠርግ ላይ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር ተገኝቶ ነበር፡፡ ‹‹ወሀለወት ህየ እሙ ለእግዚእ ኢየሱስ›› ‹‹የጌታ የኢየሱስ እናትም በዚያ ነበረች›› እንዳለ ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ (ዮሐ 2÷1)

እመቤታችን ለሠርገኞቹ ዘመድ ነበረችና ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ በሰርጉ ላይ ታድማ ነበር፡፡ እናትን ጠርቶ ልጅን መተው ሥርዓት ስላልሆነ፤ በተጨማሪ ደግሞ ደቀ መዛሙርቱ ከጌታ ጋር በሰርጉ ታድመዋል፡፡ ይህም
መምህርን ጠርቶ ደቀ መዛሙርቱን መተው ሥርዓት ስላልሆነ (ተገቢ ስላልሆነ) ነው፡፡ የሠርጉ ሥነ-ሥርዓት በሠመረ ባማረ ሁኔታ እየተከናወነ ሳለ ድንገት የወይን ጠጅ አለቀ፡፡ አስተናባሪዎቹ በጭንቀት ባሕር ሰጥመው ምን እንደሚያደርጉ ግራ በገባቸው በጠበባቸው ጊዜ የችግር ጊዜ ደራሽ የኃዘን ጊዜ አፅናኝ የሆነችው የአምላክ እናት ድንግል ማርያም ቅዱስ ገብርኤል እንደተናገረ በፀጋ የተሞላች ናትና (ሉቃ 1÷28) ማንም ሳይነግራት የልቦናቸውን ጭንቀት
አይታ፣ ጎዶሎአቸውን ተመልክታ ዘወር
ብላ ‹‹ወይንኬ አልቦሙ›› ‹‹ወይን ጠጅ እኮ አልቆባቸዋል›› አለችው፡፡

እርሱም መልሶ ‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› ‹‹ ›› አላት፡፡ እመቤታችንም ለአገልጋዮቹ ‹‹ ›› አለቻቸው/ #አማለደቻቸው፡፡ ጌታም በቦታው የነበሩ ስድስት ጋኖች ውኃ ሞልተው እንዲያመጡ አዘዛቸው፡፡ ውኃውንም ወደ ወይን ለውጦ ለሊቀ ምርፋቅ (ለአሳዳሪው) እንዲሠጡት አዘዘ፡፡
አሳዳሪውም ወደ ወይን የተለወጠውን ውኃ በቀመሰ ጊዜ አደነቀ፡፡

ከወዴት እንደመጣ ስላላወቀ ሙሽራውን ‹‹ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል ከሰከሩም በኋላ መናኛውን ያቀርባል አንተ ግን መልካሙን እስከ አሁን
አቆይተሃል›› አለው፡፡ ወይኑም በሰው እጅ ያይደለ በሠማያዊው አባት የተዘጋጀ ስለነበር ጣፋጭ እና ልብን የሚያስደስት ነበር፡፡

‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› ይህንን የጌታችንን ንግግር ብዙዎች በዘመናችን ሲሣሣቱበት ይታያል፡፡ ክብር ይግባውና አምላካችን ይህንን የተናገረው እናቱን ሊያቃልል ሽቶ አይደለም፡፡ ስለሆነም ከመጽሐፍ ቅዱስ አንፃር ይህን አረፍተ ነገር መመልከቱ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡
በተናጠል ስንመለከት ‹‹አንቺ ሴት›› ሴት የሚል ቃል የፆታ
መጠሪያ ነውና በፆታዋ አክብሮ ሲጠራት ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሔዋን ከአዳም በተፈጠረች ጊዜ አዳም እንዲህ ሲል ተናግሮ ነበር ‹‹ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት ሥጋም ከሥጋዬ ናት እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል›› (ዘፍ 2÷23

19/01/2026

ሕዝቡን፦ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦትና ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ፥ ከሰፈራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት። – ኢያሱ 3:3

የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በታቦቷ ጽፋ ክብር የምትሠጥ የሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን #ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብቻ ናት !!!

የኦሪት ጽላት እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን የሚያነጋግርበት በደመና ተከናንቦ ለእስራኤል ብቻ በረድኤት የሚገለጥበት ዙፋን ነበር ፡፡

ይህ የሐዲስ ኪዳኑ ታቦት ግን የአምላክ ሥጋና ደም የሚፈተትበት ( ጌታችን ) ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው ሥጋዬን ብሉ ደሜን ጠጡ እያለ ያመኑትን የሚጠራበት የምሕረት ምሥዋዕ ( መሠዊያ ) ነው ፡፡

እናም ለታቦት ክብርና ስግደትም የሚደረግለት ለዚህ ነው በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት በታቦታቱ ሁሉ ላይ የተጻፈው ‹‹ አልፋና ኦሜጋ ›› የሚለው የመድኃኔዓለም ክርስቶስ ስም ነው ፡፡

ከስሙ ጋር ደግሞ በሁሉም ታቦታት ላይ የሚከተለው ጥቅስ በግእዝ ተጽፎአል ፡፡ ‹‹ ከመ ለስሙ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይስግድ ኲሉ ብርክ ዘበሰማያት ወዘበምድር ›› ‹‹ ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ ›› የሚል ነው ፡፡ (ፊልጵ 2 ፡ 10 )

በታቦቱ ፊት የሚሰግድ ሰው ለምን እንደሚሰግድ በታቦቱ ላይ የሚጻፈው ይህ ጥቅስ ያስረዳናል ምክንያቱ ‹‹ ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይሰግዱ ዘንድ ›› ስለሚገባ ነው ፡፡

የክርስቶስ ሥጋ እንደሚቆረስ ደሙ እንደሚፈስስ የሚያምን ሰው በዚህ መሠዊያ ፊት በፍርሃት ለክርስቶስ ይሰግዳል ፡፡

ሥጋ ወደሙን ‹‹ ተራ መታሰቢያ ብቻ ነው ›› የሚል ሰው ግን በመሠዊያው ፊት እንዲሰግድና መሠዊያውን እንዲያከብር አንጠብቅም ፡፡

የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በታቦቷ ጽፋ ክብር የምትሠጥ የሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን ልጆች ስለሆንን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን ፡፡ ለከተራ በዓል እንኳን አደረሰን አደረሳቹ

✎﹏ዳዊት ተስፋዬ
ጥር 10 2018 ዓ.ም

Address

Sagure
Dubai

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hatersata posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Hatersata:

Share